Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመደገፍ 8 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር መደበ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመደገፍ 8 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር መመደቡን አስታወቀ።
የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በአምስት የተለያዩ የስልጠና ማእከላት ከ2 ሺህ 500 በላይ ሰልጣኞች የሚሳተፉበት የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ተጀምሯል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው እንደተናገሩት ባንኩ በ2013 በጀት ዓመት 8 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በመመደብ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በዕውቀት ላይ የተመሠረቱና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የተመደበው ገንዘብ ወጣቶችን ስራ ፈጣሪ በሚያደርግ መልኩ ለማሽነሪ ግዥ ፕሮጀክቶች እና ለሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች እንደሚውልም ነው የጠቆሙት።
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበይነ-መረብ ባስተላለፉት መልእክት ባለፈው ስርዓት ኢኮኖሚው በውስን አካላት ቁጥጥርና ቅብብሎሽ ስር መቆቱን አስታውሰዋል።
ይህም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለሀገር ኢኮኖሚ የሚጠበቅባቸውን ያህል አበርክቶ እንዳይኖራቸው አድርጓል ብለዋል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፤ ኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪና ብቁ ለማድረግ እያከናወነ ያለውን ስራ አድንቀዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ባንኩ ኢንተርፕራይዞችን ለሀገራዊ ለውጥ ብቁ ለማድረግ እያከናወነ ያለው ጥረት ለሌሎች ተቋማት ጥሩ ተሞክሮ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version