በኢትዮጵያ ቡና ላኪ ኩባንያዎችና በአልጄሪያ ቡና አስመጪ ድርጅቶች መካከል የንግድ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጀርሰ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት በኢትዮጵያ ቡና ላኪ ድርጅቶችና በአልጄሪያ ቡና አስመጪ ድርጅቶች መካከል በበይነ መረብ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ በአልጀርስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሙሉሥልጣን አምባሣደር ነብያት ጌታቸው ኤምባሲው በሁለቱ ሃገራት መካከል በተለይ የንግድ ልውውጥና ኢንቨስትመንት በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ የቅርብ ክትትል በማድረግ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የዛሬው ውይይትም ኤምባሲው ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም ካካሄደው አጠቃላይ የኢትዮጵያ የወጪ ምርቶች ማስታወቂያ መድረክ ቀጣይ ምዕራፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ቀደም ሲል በተካሄደው የወጪ ምርት ማስተዋወቂያ መድረክ ላይም በተለይ ከኢትዮጵያ ቡና ለማስመጣት ፍላጎት ያላቸውን በመለየት ለቀጣይ ግብይት የሚያመች የመረጃ ልውውጥ ማካሄጃ መድረክ መሆኑን ከአልጀርስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን