ስፓርት

ቻድ ከ2021ዱ የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ታገደች

By Tibebu Kebede

March 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቻድን ከ2021ዱ የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ማገዱን አስታወቀ፡፡

ካፍ ውሳኔውን ያስተላለፈው የሀገሪቱ መንግስት የቻድን እግር ኳስ ማህበር በይፋ ማፍረሱን ተከትሎ ነው፡፡

የቻድ ብሄራዊ ቡድን ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ከናሚቢያ እሁድ ደግሞ ከማሊ ጋር የነበረውን ጨዋታ በፎርፌ 3ለ0 እንዲሸነፉ መወሱኑንም ነው ካፍ ያስታወቀው፡፡

የካፍን ውሳኔ ተከትሎ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) በሀገሪቱ እግር ኳስ ማህበር አመራሮች ምርጫ ላይ የቻድ መንግስት ጣልቃ በመግባቱ እገዳ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ካሜሩን የምታስተናግደው 33ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ በመጭው ሰኔ እና ሀምሌ ወር ለማካሄድ ቀጠሮ ቢያዝለትም፥ በወቅቱ በሚኖረው የአየር ፀባይ ሁኔታ ምክንያት ወደ ቀጣዩ አመት ጥር እና የካቲት ወር ተዛውሯል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!