የሀገር ውስጥ ዜና

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

By Abrham Fekede

March 22, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በሚያካሂደው 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

በስብሰባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች  ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የምክር ቤቱን 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን