አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮንጎው ፕሬዚዳንታዊ እጩ ተወዳዳሪ ጋይ ብሪስ ኮለላስ ምርጫው ከተካሄደ ከአንድ ቀን በኋላ በኮቪድ ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
እጩ ተወዳዳሪው ወደ ሆስፒታል የገቡት ምርጫ በሚካሄድበት ዋዜማ እንደነበረም ተነግሯል፡፡
ይህንንም ተከትሎ ለተጨማሪ ህክምና ወደ ፈረንሳይ በማቅናት ላይ ሳሉ አውሮፕላን ውስጥ ህይወታቸው አልፏል፡፡
በኮንጎ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን መራጮች ተመዝግበዋል፡፡
የ77 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሱዎ ንገሶ ሃገሪቷን ለ36 ዓመታት መርተዋል፡፡
ትናንት በተካሄደው ምርጫም የማሸነፍ ቅድሚያ ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲና አልጀዚራ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን