አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር መወያየታቸውን አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱን ያካሄዱት ዛሬ ጠዋት መሆኑን በማህበራዊ ገጾቻቸው ላይ ገልጸዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት ሠራዊቱ የሠላም ጠባቂ እና የሀገር ሉዓላዊነት የሚያስከብር በመሆኑ ኩራት እንደሚሰማቸው ነው ያስታወቁት፡፡
ስነ ምግባርን እና ሙያተኝነትን የማጠናከር እና በየትኛውም የሕግ ማስከበር ሥራ የመከላከያ ሠራዊቱ እሴቶች የማይወክል ተግባር የሚፈጽሙትን ተጠያቂ ማድረግ፣ በአግባቡ ኃላፊነታቸውን የሚወጡትን መሸለም እንደሚገባም አሳስበዋል።
የተጠያቂነት እና የስነ ምግባር ክፍተቶች በተገቢው ስርዓት እርምጃ እንደሚወሰድባቸውም ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን