አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል በዋና ዋና መንገዶች እና ለሕዝብ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት ላይ የኬሚካል ርጭት ተካሄደ።
በሐዋሳ ከተማ በትናንትናው ዕለት ብቻ የኮቪድ ናሙና ከሰጡ 200 ግለሰቦች ውስጥ 68ቱ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ኮቪድ-19 በከተማዋ ሥርጭቱ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ እየተስፋፋ በመሆኑ ሕዝቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡
የከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙንጣሻ ብርሃኑ እስካሁን በከተማው በተደረገው 34 ሺህ 738 ምርመራ 4 ሺህ 275 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ይፋ አድርገዋል፡፡
በከተማዋ ያለው በኮሮና ቫይረስ የመያዝ መጣኔ 12 በመቶ ደርሷል፡፡
ረዳት ፕሮፌሰሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አገልግሎት የሚሠጡ ተቋማት አስፈላጊውን የጥንቃቄ መንገድ በመከተል አገልግሎት እንዲሲጡ ጠይቀዋል፡፡
በመንግስት እና በግል የሚደረጉ ስብሰባዎች አስፈላጊውን የኮሮና ፖሮቶኮል ሟሟላት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።
በታመነና አረጋ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!