አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሁለት ሳምንታት በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተደረገ የሕግ የበላይነት የማስከበር ስራ 21 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱንና 96 ግብረ አበሮቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የኮሙዩኒኬሽና የሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ጌታቸው ኢታና እንደገለጹት፥ የኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ህዝብና በክልሉ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች ያለ ጸጥታ ስጋት በሰላም እንዲኖሩ ለማስቻል በቂ የጸጥታ አካላትን አሰልጥኖ አሰማርቷል፡፡
ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ህብረተሰቡ ለጸጥታ አካላት መረጃ በመስጠት በኦነግ ሸኔ ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ማገዝ እንዳለበት ረዳት ኮሚሽነር ጌታቸው ኢተና ጥሪ ማቅረባቸውን ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!