Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለአዲሷ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት የድጋፍ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለአዲሷ የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሃሰን የድጋፍ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ፕሬዚዳንቷ ባስተላለፉት መልዕክት በአገራቸውና ሕዝባቸው ላይ የወደቀውን ሃዘን በመወጣት ታንዛኒያን ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለመምራት የእርሳቸው ወደ ስልጣን መምጣት ለአገራቸው ብቻ ሳይሆን ለቀጣናው እንዲሁም ለአህጉሩ ያለውን ትልቅ ፋይዳ ገልጸዋል፡፡
“ጥቂት ሴት መሪዎች ባሏት አህጉራችን ሴቶች ወደ አመራር ቦታ መምጣታቸው የሴቶች ድምፅ እንዲሰማ የሚያደርግ ብቻ ሳይሆን ሴቶች እንደሚችሉ የሚያሳይ ነው” ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ አዲሷ ፕሬዚዳንት ይህን ታላቅ ሃላፊነት በሚወጡበት ወቅት ከጎናቸው እንደሚሆኑም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version