ስፓርት

በቻምፒየንስ ሊጉ ሩብ ፍጻሜ ባየርን ሙኒክ ከፒ ኤስ ጂ ይጫወታሉ

By Tibebu Kebede

March 19, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡

ሩብ ፍጻሜው የአምናዎቹን የፍጻሜ ተፋላሚዎች ባየርን ሙኒክ እና ፒ ኤስ ጂን አገናኝቷል፡፡

ሪያል ማድሪድን ከሊቨርፑል ያገናኘው የሩብ ፍጻሜ ድልድል ተጠባቂ ሆኗል፡፡

የፔፕ ጋርዲዮላው ማንቼስተር ሲቲ ከጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርትመንድ ጋር ተገናኝቷል፡፡

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ደግሞ ከፖርቹጋሉ ፖርቶ ጋር ተደልድሏል፡፡

በግማሽ ፍጻሜው የባየርን ሙኒክ እና የፒ ኤስ ጂ አሸናፊ ከማንቼስተር ሲቲ እና ቦሩሲያ ዶርትመንድ አሸናፊ ጋር ይገናኛል፡፡

የሪያል ማድሪድ እና የሊቨርፑል አሸናፊ ደግሞ ከቼልሲ እና ፖርቶ አሸናፊ ጋር የሚገናኝ ይሆናል፡፡