Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ለፊቤላና ለሸሙ የዘይት ፋብሪካዎች 44 ሚሊየን ዶላር ብድር በልዩ ሁኔታ ሊያቀርብ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)መንግስት ለፊቤላና ለሸሙ የዘይት ፋብሪካዎች 44 ሚሊየን ዶላር ብድር በልዩ ሁኔታ ሊያቀርብ ነው::
በንግድ ሚኒስትር መላኩ አለበል የተመራ የልዑካን ቡድን በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፖርክ የሚገኘውን ሸሙ ግሩፕን ጎብኝቷል።
የተለያዩ የቤት ውስጥ ንፅህና መጠበቂያ ላርጎዎችን ጨምሮ በቀን እስከ 950 ቶን ዘይት የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካው በሀገር ውስጥ ምርቱን በማከፋፈል ላይ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው።
ፋብሪካው መሠረታዊ በሆኑ ምርቶች ላይ መሠማራቱ የሚበረታታ ነው ያሉት ሚኒስተሩ አቶ መላኩ አለበል ÷ በጉብኝቱ ወቅት የተመለከቷቸው ክፍቶች እንዲታረሙ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ፋብሪካው በበኩሉ ምርቶቹ በሚገባቸው ፍጥነት አለመነሳታቸው ካጋጠሙት ተግዳሮቶች ዋነኛው እንደሆነ ለሚኒስትሩ አብራርቶላቸዋል።
የተጠቀሱትን ችግሮች የተፈጠሩት ፋብሪካዎች ባጋጠማቸው የመስሪያ ካፒታል እጥረት ነው ያሉት ሚኒስትሩ ÷ የተጠቀሱትን ችግሮች ለመፍታት መንግስት የ44 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለፊቤላና ለሸሙ የዘይት ፋብሪካዎች በልዩ ሁኔታ ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን ተናግረዋል።
ጉብኝቱ ከሰዓት በኋላም የሚቀጥል ሲሆን በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፖርክ የሚገኙ የተለያዩ ፋብሪካዎችን ጨምሮ የናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በእዩናዳብ አንዱአለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.