Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቻይና በመንገድ ዋሻ መደርመስ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና በመንገድ ዋሻ መደርመስ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡

በሰሜን ምዕራብ ቻይና ኪንጋይ ግዛት የሚገኝ የጎዳና ዋሻ  በተፈጠረው ቀዳዳ የመንገደኞች አውቶቡስ ወደ በመግባቱ አደጋው መከሰቱ ነው የተነገረው፡፡

በስፍራው ፍንዳታ መከሰቱ የተነገረ ሲሆን ከሞቱት በተጨማሪም 16 ሰዎች መቁሰላቸው እና እነዚህም በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

በአውቶብስ ውስጥ ምን ያህል ሰው እንደነበረ ባይታወቅም የአካባቢው ባለስልጣናት አሁንም የነፍስ አድን ስራ እየተሰራ መሆኑን  ተናግረዋል ፡፡

አደጋው ወደተከሰተበት ስፍራም 1 ሺህ የነፍስ አድን ስራተኞችን ጨምሮ 30 ተሽከርካሪዎች እና ሁለት የቁፋሮ ተሸከርካሪዎች ተልከዋል ነው የተባለው፡፡

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን

Exit mobile version