የሀገር ውስጥ ዜና

12ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ፌስቲቫል ተከፈተ

By Tibebu Kebede

March 19, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 12ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ሳምንት “ባህል ለህዝቦች ሰላምና አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ነው።

በባህል ፌስቲቫሉ ላይ የተለያዩ ባህላዊ ትዕይንቶች ይቀርባሉ።

በግዮን ሆቴል እየተከበረ ባለው ከተማ አቀፍ የባህል ሳምንት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡና በባህል አልባሳት ያጌጡ ነዋሪዎች ተሳታፊዎችድ ናቸው።

በባህል ፌስቲቫሉ ላይ 150 የሚሆኑ ሀገር በቀል ምርቶች የሚቀርቡበት አውደ ርዕይ እንደሚካሄድ ኢብኮ ዘግቧል።

ጠቃሚ የሆኑ ባህሎችን መጠበቅ እና ሰላምና አንድነትን ለማጠናከር እንደ ግብዓት መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይዘሪት ፎዚያ መሀመድ ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!