የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ከጀርመኑ አቻቸው ፍራንክ ስታይንማየር ጋር ተወያዩ

By Abrham Fekede

March 18, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከጀርመኑ አቻቸው ፍራንክ ዋልተር ስታይንማየር ጋር ተወያዩ፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ የጀርመኑ አቻቸው ባደረጉላቸው የስልክ ጥሪ መሰረት መወያየታቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በውይይታቸውም በትግራይ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ አንስተው መክረዋል፡፡

እንዲሁም የኮቪድ-19 ወረርሽኝና፣ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዉይይት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!