ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሙሳ ፋኪ ማህመት በታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

By Abrham Fekede

March 18, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት በታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡

ሊቀመንበሩ አህጉሪቷ ቁርጠኛ የፓን አፍሪካኒስት መሪ አጥታለች ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በተጨማሪም በምስራቅ አፍሪካ ባለው ቀጠናዊ ትብብር ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸውም ነው ያስታወሱት፡፡

ሊቀመንበሩ ለታንዛኒያ ሕዝብና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

ጆን ማጉፉሊ ሌሊቱን ለህልፈት መዳረጋቸውን የሃገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ይህንን ተከትሎም በሀገሪቱ የ14 ቀናት ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታውጇል፡፡

በታንዛኒያ አንድ በስልጣን ላይ የሚገኝ መሪ ሕልፈት ሲሰማ ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቷ ሳሚያ ሐሰን ስድስተኛዋ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት በመሆን ስልጣን እንደሚይዙ ይጠበቃል፡፡

በአህጉሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የአፍረካ ሃገራት መሪዎች ሐዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ማጉፉሊን አፍሪካዊነትን የሚያቀነቅኑ መሪ እንደነበሩም አስታውሰዋል፡፡

ኡሁሩ በኬንያ ለሰባት ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን አውጀዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2015 ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ሁለተኛውን የስልጣን ዘመናቸውን የጀመሩት ባለፈው ጥቅምት ወር መጨረሻ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!