አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ እጩዎች የሚኖራቸው ቅደም ተከተል በሎተሪ ዕጣ እንደሚወሰን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ ።
ይህም የድምጽ አሰጣጥ ሂደትን ግልጽነት እና ፍትሐዊነት ለመጨመር እንደሚያስችል ታምኖበታል።
ሂደቱ ሁለት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው በእጅ ( ማንዋል ) ሲሆን ሁለተኛው ሂደት በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ሲስተም የሚከናወን ነው ተብሏል።
በመጀመሪያው ደረጃ የዕጩዎች ስም፣ የፓርቲ ስም እና ቁጥር ያለበት ዝርዝር ፖስታ የያዙ የዕጣ ማውጫ ሳጥኖች ይዘጋጃሉም ነው የተባለው ።
ለተወካዮች ምክር ቤት እያንዳንዱ ዕጩ በተናጥል የሚታይ ሲሆን ለክልል ምክር ቤቶች የግል ዕጩዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ አንድ ብሎክ እንደሚታዩ ተነግሯል።
በብሎክ ውስጥ ያሉ ዕጩዎች በተዘበራረቀ መንገድ እንደሚቀመጡ ቦርዱ ገልጿል ።
የማንዋል ሂደቱ ውጤት አውቶማቲክ ወደ ሆነ የድምፅ መስጫ ወረቀት ማዘጋጃ ስርዓት ይገባልም ነው የተባለው።
በዓላዛር ታደለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!