አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስምንት ወራት 191 ነጥብ 45 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ በስምንት ወራት ውስጥ 191 ነጥብ 28 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ከእቅድ በላይ መሳካት መቻሉንም አስታውቋል፡፡
ገቢው ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ24 ነጥብ 63 ቢሊየን ብር ጭማሪ አሳይቷል፡፡
ከተገኘው ገቢ ውስጥ የሀገር ውስጥ ታክስ 116 ነጥብ 70 ቢሊየን፣ የውጭ ቀረጥና ታክስ 74 ነጥብ 59 ቢሊየን ብር እንዲሁም ከሎተሪ ሽያጭ የተጣራ ገቢ ብር 154 ነጥብ 46 ሚሊየን መሰብሰቡን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!