የሀገር ውስጥ ዜና

140 ዜጎች ከየመን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Abrham Fekede

March 16, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 140 ዜጎች በዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አማካኝነት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ለመመለስ ፍቃደኛ የሆኑትን ዜጎች ነው ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ማመቻቸቱን የገለጸው፡፡

ይህም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ነው ድርጅቱ ያስታወቀው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃልአቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው ሳምንታዊ መግለጫቸው ላይ ከየመን ዜጎች እንደሚመለሱ አስታውቀው ነበር፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!