Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ወደ መዲናዋ እየገባ ያለው ምርት ለታለመለት አላማ እና ለታሰበለት ህዝብ መዋል አለበት-ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የሸማቾች ማህበራት ጋር እየታየ ያለውን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ በተሰሩ ስራዎች ላይ ውጤት ማየት መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡
ምክትል ከንቲባዋ የእህል ምርት በይበልጥ ጤፍ በብዛት ወደ አዲስ አበባ እንዲገባ የተሰራው ስራ የግብይይት ሰንሰለት በማሳጠር እንዲሁም አቅርቦት በመጨመር የገበያ መረጋጋትን ለማየት ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡
ወደ ከተማ እየገባ ያለው ምርትም ለታለመለት አላማ እና ለታሰበለት ህዝብ መዋል አለበት ያሉት ወይዘሮ አዳነች ሕብረተሰቡ ይህን ተረድቶ በአቅራብያው ባሉ የሸማች ማህበራት ሄዶ በመሸመት እና በተለያዩ መንገዶች ነዋሪውን የሚያጉላሉትን ነጋዴዎችን በማጋለጥ ሃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል።
በሌላ በኩል የህብረት ስራ ዩኒየኖችን እና የሸማቾች ማህበራትንም የተሰጣቸዉን ገንዘብ በቀጥታ እና በታማኝነት ለተባለው አላማ በማዋል ለተጫወቱት አውንታዊ ሚና ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version