የሀገር ውስጥ ዜና

በግለሰብ ቤት ተከማችቶ የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ

By Abrham Fekede

March 15, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በግለሰብ ቤት ተከማችቶ የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ፡፡

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጭኮ ከተማ አስተዳደር እና በሀዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለ ከተማ ነው የጦር መሳሪያ መያዙን የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ ለገሰ ያስታወቁት፡፡

በጭኮ ከተማ ላይ በተደረገው ክትትል 30 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ እና ሁለት መትረየስ ተይዟል፡፡

በተመሳሳይ ሀዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለ ከተማ ፋራ ቀበሌ ልዩ  ቦታው ወልደ አማኑኤል ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ በሚገኝ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ የፌደራል ፖሊስ እና የክልሉ ልዩ ሀይል በጋራ ባደረጉት ፍተሻ 98 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ከ4 ሺህ 583 መሰል ጥይት ጋር መያዙ ነው የተገለጸው፡፡

እንዲሁም 3 ሺህ 546 የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት ከሶስት ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙሉን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!