Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሜሪካ ከ100 ሚሊየን በላይ ዜጎቿን የኮቪድ19 ክትባት ሰጠች

Mary Lou Russler receives a coronavirus disease (COVID-19) vaccine during a community vaccination event in Martinsburg, West Virginia, U.S., March 11, 2021. REUTERS/Kevin Lamarque

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ከ100 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎቿ ቢያንስ አንድ ጊዜ የኮቪድ19 ክትባት መስጠቷን አስታወቀች፡፡

የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ክትባቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ በስፋትና በፍጥነት ለማዳረስ እየጣረ ነው ተብሏል፡፡

ባይደንም በንግግራቸው በ100 ቀናት አሳካለሁ ያልኩትን በ60 ቀናት ውስጥ አሳክቻለሁ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህም በወረርሽኙ የሚያዙ አሜሪካውያን ቁጥር እየቀነሰ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ክትባቱን ከወሰዱት 100 ሚሊየን አሜሪካውያን ውስጥ 35 ሚሊየን የሚሆኑት ሁለት ጊዜ  ወስደዋል፡፡

እስከ ግንቦት ድረስ ሁሉም አዋቂዎች እንደሚከተቡ የጠቀሱት ባይደን ሀገራቸው በነጻነት ቀኗ ጁላይ 4 ወደ መደበኛ ህይወት ትመለሳለች ብለዋል፡፡

እስካሁን ከ29 ሚሊየን በላይ ዜጎቿ በወረርሽኙ የተያዙባት አሜሪካ 532 ሺህ ዜጎቿ ደግሞ በዚሁ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡-ዘ-ዎል-ስትሪት-ጆርናል

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

Exit mobile version