Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከ610 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ ምርቶች ወደ ውጭ ተልከዋል- የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ተገንብተው ወደ ሥራ ከገቡ 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች እስካሁን ከ610 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ መቻሉን ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
የኮርፖሬሽኑ ማርኬቲንግና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ በኃይሉ ከበደ እንደገለፁት የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ያመረቱትን ወደ ውጭ በመላክ እና የሥራ እድል በመፍጠር የተሰጣቸውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት የማምጣት ተልእኮ ማሳካት ችለዋል።
በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ የሚመረቱት የአልባሳትና ሌሎች ምርቶች ለውጭ ገበያ ተብለው በትእዛዝ እንደሚመረቱ የገለፁት ኃላፊው የአውሮፓ፣ አሜሪካ እና ሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ ሸማቾችም ስለጥራታቸው መመስከራቸውን ገልፀዋል።
በ13ቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ከ89 ሺህ በላይ የሥራ እድል መፈጠሩንም ነው አቶ በኃይሉ የተናገሩት።
በሌላ በኩል የፓርኮቹን ሰራተኞች የሚያጋጥማቸውን የኑሮ ውድነት፣ የመኖሪያ ቤት፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ችግሮች ለመፍታት እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል።
በኢትዮጵያ አዲስ እየተገነቡ ባሉት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከመብራትና መንገድ እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማቶችን በጊዜአዊነትና በቋሚነት ለማሟላት እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረው በዚህም የኃይል መቆራረጥ ችግር ከ95 በመቶ በላይ መሻሻል ማሳየት መቻሉን ነው የገለፁት።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ በፓርኮቹ የሚገነቡ የመብራት፣ መንገድና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን የሚያስተጓጉሉ የካሳ እና ሌሎች ጉዳዮች እንዲፈቱ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው እንዲያግዙ ኮርፖሬሽኑ ጥሪ አቅርቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version