አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለታንዛኒያ የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ በአፍሪካ ህብረት ጽህፈት ቤት ሃውልት ሊቆም ነው፡፡
ኔሬሬ የአፍሪካ አንድነትን በኋላም የአፍሪካ ህብረትን ከመሰረቱ መሪዎች መካከል አንደኛው ናቸው፡፡
ሃውልቱን የሚያቆመው የደቡብ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ /ሳዴክ/ እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡
ሳዴክ በቅርቡ የተመሰረተበትን 40ኛ ዓመት ያከብራል፡፡
ከአምስት ዓመታት በፊት የጀርመን መንግስት በመደበው 27 ሚሊየን ዩሮ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና ፅህፈት ቤት ግቢ ውስጥ የጁሊየስ ኔሬሬ የሰላምና ፀጥታ ህንፃ መመረቁ ይታወሳል፡፡
ህንፃው የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት የሚወያይበት አዳራሽ፣ በአህጉሪቱ የሚያጋጥሙ አስቸኳይ የፀጥታ ሁኔታዎች የሚታዩባቸው ክፍሎች እና ቤተ መፅሃፍትን አካቷል፡፡
ጁሊየስ ኔሬሬ በአውሮፓውያኑ 1961 የታንጋኒካ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን የተመረጡ ሲሆን በኋላም ታንጋኒካ ከዛንዚባር ጋር መዋሃዷን ተከትሎ በ1964 የታንዛኒያ የመጀመሪው ፕሬዚዳንት በመሆን መመረጣቸው ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!