Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የማሽላ ምርምር በአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ በመተግበር ላይ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2012 (ኤፍቢሲ) የማሽላ ምርምር በአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ በመተግበር ላይ መሆኑ ተገለጸ።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ድጋፍ የሚካሄደው ምርምር፥ አንድ ጊዜ ተዘርቶ ዳግም ሳይታረስና ሳይዘራ በአመት እስከ ሶስት ጊዜ በአማካይ በሄክታር ከ60 እስከ 70 ኩንታል ምርት መስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተደገፈ ጊዜ ጀምሮ ከዚህ ቀደም በሁለት የተለያዩ ጣቢያወች ሙከራ ተደርጎበት አመርቂ ውጤት ታይቶበታልም ነው የተባለው።

ምርምሩ እየተተገበረበት ባለው አካባቢ ባለፈው ሰኔ ወር ከተዘራ ጀምሮ ለሶስተኛ ጊዜ የሰጠው ምርት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮች በትናንትናው እለት መጎብኘቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version