Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ የ6 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የጋራ ገበያ የድንበር አካባቢዎችን ለማልማት የ6 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ።

በስምምነቱ መሰረት ድጋፉ የድንበር አስተዳደር፣ በሞያሌ እና ጋላፊ ኬላ ንግድና ትራስንፖርት ለማሻሻል  እንደሚውል ተጠቁሟል።

ይህም ኢትዮጵያ የአንድ መስኮት አገልግሎትን እንድታሻሽል፣ በኤጀንሲዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ለመጨመር፣ በሞያሌ እና ጋላፊ የሚገኙ ጉምሩክ ቅርንጫፎችን ግንኙነት ለማሳደግ እንደሚያስችላት ነው የተነገረው።

ለፕሮጀክቱ በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ በኩል የአውሮፓ ህብረት ድጋፍ እንደሚያርግ አፍሪካ ቢዝነስ ኮሚዩኒቲ ዘግቧል።

ስምምነቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታ ምስጋኑ አረጋ እና የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ ዋና ፀሃፊ ቺሌሺ ካፕውፕዌ ተፈራርመዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.