የሀገር ውስጥ ዜና

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

January 13, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 4 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሞሃመድ ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፒተር ማውራ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በክልሉ በጎሳ ግጭት ምክንያት ለተጎዱ ሰዎች እያደረገ ባለው ድጋፍ ላይ መክረዋል።

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፒተር ማውራ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት በጅግጅጋ ጀምረዋል።

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ለ11 አመታት በሶማሌ ብሔራዊ ክልል የሚያቀርበውን ሰብዓዊ ድጋፍ አቋርጦ እንደነበር የሚታወስ ነው።

የክልሉ አስተዳደር ሰብዓዊ ድጋፉ ይቀጥል ዘንድ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ከፈረንጆቹ 2018 ጀምሮ ድጋፉን በድጋሚ አስጀምሯል።