አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ዛሬ በአማራ ክልል 5 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ባስጀመሩበት ወቅት ነው፡፡
የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታን ያስጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣዩ ምርጫ ግባችን ኢትዮጵያን አሸናፊ የሚያደርግ ምርጫ ማካሄድ ነው ብለዋል።
የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ የሆነ ለሁሉም እኩል እድል ተፈጥሮ ሀሳብ በነፃነት የሚንሸራሸርበት እንደሚሆንም ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝቡ ባስተላለፉት መልዕክት በምርጫው ያሻችሁን ምረጡ ግን ሰላምን አስቀድሙ፤ ያሻችሁን ምረጡ ግን እኩል መድረክ መፈጠሩን አረጋግጡ ሲሉም ተናግረዋል።
ይህ ሲሆን ኢትዮጵያ ታሸንፋለች ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
በምርጫዉ ብንሸነፍ ለአሸናፊው አቅፈን ስልጣን በማስረከብ አዲስ ታሪክ እንሰራለን ካሸነፍን ደግሞ ኢትዮጵያ ወደሚገባት ብልጽግና ለማውጣት ቀን ከሌት እንሰራለን ብለዋል::
ኢትዮጵያ ለመላው የአፍሪካ ሀገራት የነጻነት ተምሳሌት እንደሆነችው ሁሉ ይህ ትውልድም ጠንክሮ ሰርቶ በልማት በአፍሪካ አርዓያ ሊሆን ይገባዋል ነው ያሉት።
በአላዛር ታደለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/…/www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!