Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሴቶች የተሻለ ቦታ እንዲደርሱ በትምህርት ቤቶች ምቹ ሁኔታን መፍጠር ይገባል – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ቱሉ ዲምቱ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ በትምህርት ቤት ውስጥ እየተደረገ ስላለው የሴት ተማሪዎች ድጋፍ እና የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ገለፃ ተደርጓል።
በትምህርት ቤት ውስጥ ባሉት የልዩ ፍላጎት እና የስነ ልቦና ድጋፍ መስጫ ክፍሎች ጉብኝት የተደረገ ሲሆን በባለሙያዎች ስለሚሰጠው አገልግሎትም ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በትምህርት ቤት ውስጥ የስርአተ ፆታ ክበብ በማቋቋም ጥቃቶችን ለመከላከል እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን ገልፀው በቀጣይነትም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል።
ትምህርት ቤቱ ለሴት ተማሪዎች ምቹ ሁኔታን የፈጠረ በመሆኑ ሌሎች ትምህርት ቤቶችም ይህን አርዓያ ሊከተሉ እንደሚገባ ጠቅሰው ሴት ልጅ የተሻለ ቦታ እንድትደርስ የሁሉም ድጋፍ ያስፈልጋልታልም ነው ያሉት፡፡
የነገ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሴቶች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን መናገራቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version