Fana: At a Speed of Life!

ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበር አርአያ ሊሆኑ ይገባል – አቶ ላቀ አያሌው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልህቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል አሉ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ከግብር ከፋዮችና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው፤ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ሀሰተኛ ደረሰኝ ከመጠቀምና ሀሰተኛ ኪሳራ ከማሳወቅ በመቆጠብ ለታክስ ህግ ተገዢ በመሆን ዘመናዊ የንግድ ስርዓት በማስተዋወቅ የልህቀት ማዕከል ሊሆኑ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በሰባት ወራት ውስጥ ከተሰበሰበው ጠቅላላ ገቢ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ድርሻ 50 በመቶ ከሀገር ውስጥ ገቢ ደግሞ 80 በመቶ ድርሻ አለው ነው ያሉት፡፡

የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ተሬሳ እንሴሱ በበኩላቸው ቅ/ጽ/ቤቱ በሰባት ወራት ውስጥ 79.98 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 108 በመቶ ማሳካቱን እንዲሁም በፌደራል ደረጃ ተሸላሚ ለነበሩ 150 ግብር ከፋዮች ልዩ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ማጭበርበርና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ገዙ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ከዕቅድ አንጻር የሚሰበሰበው ገቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገት ቢያሳይም ወጪን ከመሸፈን አንጻር የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉ ገልጸዋል፡፡

በ2012 በጀት ዓመት በታክስ ገቢ የሀገሪቱን 48 በመቶ ብቻ ወጪ እንደሸፈነና ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ገቢ 8.66 በመቶ ብቻ እየተሰበሰበ ሲሆን ለዚህም ዋነኛው ምክንያት የታክስ ህግ ተገዢነት ችግር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.