የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ ገቢን ለማምጣት እየሰራች ነው-ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ

By Abrham Fekede

February 25, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍን በማልማት ከፍተኛ ገቢ ለማግኘት እየሰራች እንደምትገኝ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ገለጹ።

በዓለም አቀፉ የባቡር ትራንስፖርት ድርጅት ዩ አይ ሲና በኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መንገድ የተዘጋጀ የዌቢናር ውይይት “የባቡር ትራንስፖርት አጋርነት በአፍሪካና የዘርፉ የልማት ዕይታዎቹ ” በሚል እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ “ኢትዮጵያ የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍን በማልማት ከፍተኛ ገቢ ለማግኘት እየሰራች ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም ከዘርፉ ከፍተኛ ጥቅም ለማግኘት ከዓለም አቀፍ ተቀማትና አጋር አካላት ጋር በጋራ እየተሰራ እንደሚገኝ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በዘርፉ ከተሰማሩ ተቋማት ጋር የሚካሄደው ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመጠቆምም የግንኙነቱ መጠናከር የአሰራር ብቃትን እንደሚያሻሽልና የማጓጓዝ አቅምን እንደሚያጎለብት አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!