የሀገር ውስጥ ዜና

በጂቡቲ የተገነባው የኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ተመረቀ

By Tibebu Kebede

February 18, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጂቡቲ የተገነባው የኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ተመረቀ፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስትር ዲኤታው አቶ አወል ወግሪስ የተሽከርካሪ ማቆሚያው ግንባታ እያደገ ከመጣው የወጪ ገቢ እቃዎች አንጻር እየጨመረ የመጣውን የአገልግሎት ፍላጎት ለማሟላት መንግስት ያለውን ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለውታል፡፡

ከዚህ ባለፈም የሁለቱ እህትማማች ሃገራት ግንኙነት በኢኮኖሚያዊ ትስስር እየተጠናከረ መሄዱን ያሳያልም ነው ያሉት፡፡

የጁቡቲ መንግስት ለማቆሚያው እና ለማስፋፊያው ግንታ ላደረገው ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ያስገነባው የተሽከርካሪ ማቆሚያ ግንባታ መጠናቀቅ፥ የተሽከርካሪዎችን መጨናነቅን በማስቀረት የተሳለጠና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡

በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ የትራንስፖረት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አወል ወግሪስ፣ በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ የጂቡቲ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚኒስትር ሙሳ ሞሃመድና የሃገራቱ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!