Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገነባው ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የግንባታ ቅድመ ዝግጅት ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገነባው ግዙፍ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የግንባታ ቅድመ ዝግጅትን በተመለከተ በገንዘብ ሚኒስቴር ውይይት ተካሂዷል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ጋር በኢትዮጵያ ሁለተኛው ሜጋ ፕሮጀክት በሆነው አዲሱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የግንባታ ቅድመ ዝግጅት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በዚሁ ወቅት አዲሱ ፕሮጀክት የኢትዮጵያን የአውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሻግር ተመላክቷል፡፡

ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን የኢትዮጵያን የአየር ትራንስፖርት ተጓዦች እና የካርጎ መናኸሪያ በማድረግ የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ተብሏል፡፡

ለኢትዮጰያ ዘላቂ ልማትና እድገት ትልቅ ሚና እንደሚጫወትም ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

በውይይቱ ወቅት ከዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያው በተጨማሪ በዕቅድ በተያዙ አምስት የአውሮፕላን ማረፊያዎች እና ተርሚናሎች የማስፋፋት ስራዎች መሰናዶ ላይ መግባባት ላይ መደረሱን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.