ስፓርት

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ፒ ኤስ ጂ እና ሊቨርፑል ድል ቀንቷቸዋል

By Tibebu Kebede

February 17, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ተጀምረዋል፡፡

በምሽቱ ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ ፒ ኤስ ጂ እና ሊቨርፑል ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በካምፕ ኑ ባርሴሎና ከፒ ኤስ ጂ ባደረጉት ጨዋታ የፈረንሳዩ ክለብ በሰፊ የጎል ልዩነት ባርሴሎናን አሸንፏል፡፡

በጨዋታው ባርሴሎናዎች ባገኙት የፍጹም ቅጣት ምት ጨዋታውን መምራት ቢችሉም በኪሊያን ምባፔ ሶስት እንዲሁም በሞይስ ኪን 1 ጎል ፒ ኤስ ጂ ጨዋታውን 4 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ኪሊያን ምባፔም በጨዋታው ሐት ትሪክ ሰርቷል፡፡

በሌላኛው ጨዋታ ደግሞ ከሜዳው ውጭ ከጀርመኑ አር ፒ ሌፕዚግ ጋር የተጫወተው ሊቨርፑል 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡

በጨዋታው ሞሃመድ ሳላህ እና ሳዲዮ ማኔ ለሊቨርፑል የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!