የሀገር ውስጥ ዜና

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Abrham Fekede

February 16, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር ራፋኤል ሞሮቭ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም በትምህርት፣ ዲፕሎማሲ፣ ኢንቨስትመንት፣ በባህልና ቱሪዝም ዘርፎችን በተመለከተ መክረዋል፡፡

እንዲሁም ከእስራኤል ከተሞች ጋር እህትማማችነት መፍጠርን ጨምሮ ተባብረው ለመስራት በሚያስችላቸው ሁኔታዎች ላይ መነጋገራቸው ነው የተገለጸው፡፡

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ብሎም በመዲናዋ ለሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ያላቸውን አክብሮት በዚሁ ወቅት ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም በከተማዋ እና በእስራኤል መንግስትና ህዝብ መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት እና ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እና ተቀራርበው ለመስራት ዝግጁ ነን ብለዋል።

አምባሳደር ሞሮቭ በበኩላቸው የኢትዮጵያና እስራኤልን ለዘመናት የቆየ ግንኙነት እና ትብብር አድንቀዋል፡፡

በቀጣይም በተወያዩባቸው ዘርፎች በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፅኑ ፍላጎት መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!