ኮሮናቫይረስ

ቻይና የለገሰችው የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባት ዚምባብዌ ገባ

By Abrham Fekede

February 15, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የለገሰችው የመጀመሪያው ዙር የኮሮና ቫይረስ ክትባት ዛሬ ጠዋት ዚምባብዌ ዋና ከተማ ሐራሬ መግባቱ ተሰምቷል፡፡

የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮንስታቲኖ ቺዌንጋ፤ ሮበርት ጋብሬል ሙጋቤ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን በመገኘት ድጋፉን ተቀብለዋል፡፡

ከምክትል ፕሬዚዳንቱ በጨማሪ በዚምባብዌ የቻይና አምባሳደርም ተገኝተዋል፡፡

ቻይና የለገሰችው የኮሮና ቫይረስ ክትባት 200 ሺህ መጠን ያለው ነው ተብሏል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ክትባቱ የበለጸገው ሲኖፋርማ በተባለው የሀገሪቱ ብሔራዊ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ መሆኑም ተነግሯል፡፡

 

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!