አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርክ በኢትዮጵያ በተጨማሪ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የመሰማራት ፍላጎት እንዳላት በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራቅ አልፕ ተናገሩ፡፡
ቱርክ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያፈሰሰችው መዋዕለ ነዋይ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር እንደሚደርስ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
የሃገሪቱ ባለሃብቶችም በኢትዮጵያ በጨርቃጨርቅ እና ሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ ሲሆን፥ ከቻይናውያን ባለሃብቶች በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ቱርክ ዛሬ ያቀናሉ፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን በቱርክ በሚኖራቸው ቆይታ ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽ፣ በቀጠናዊ እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ የተገነባውን አዲሱን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መርቀው ይከፍታሉ ተብሏል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.FanaAm በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!