አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በመቀሌ ከተማ ለሚገኙ ተማሪዎች ከ50 ሺህ በላይ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።
የስፖርት ማህበሩ ተወካዮች ቡድን የተለያዩ የትምህርት መማሪያ ቁሳቁሶችን በከተማው በመገኘት ለከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ለአቶ አታክልቲ ኃይለሥላሴ አስረክበዋል ።
ድጋፉን የተረከቡት ከንቲባው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር እንደ እግር ኳሱ በማህበራዊ ዘርፎችም ቀዳሚ በመሆን የሚያከናውናቸው ተግባራት እጅግ የሚበረታቱና በአርአያነት የሚያስነሳው ነው ብለዋል ።
በተለይም የመቀሌን ህዝብ ፍቅር ሳትረሱ በዚህ ወቅት በትክክለኛው ሰዓት በሚያስፈልገን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ስላደረጋችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው በማለት ገልጸዋል።
በቀጣይም ይህ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመጠየቅ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተሰቦችን በከተማቸው ዳግም የምንከባከብበት ቀን ሩቅ አይሆንም በማለት መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከስፖርት ክለቡ የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!