Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የቶኪዮ ኦሊምፒክ ሃላፊ ዮሺሮ ሞሪ ከሃላፊነት ለቀቁ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቶኪዮ ኦሊምፒክ ሃላፊ ዮሺሮ ሞሪ ከሃላፊነት ለቀቁ፡፡

ሃላፊው ከዚህ በፊት”ሴቶች ብዙ ያወራሉ” በማለት ሴቶችን ባልተገባ መልኩ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

የ83 አመቱ አዛውንት “ሴት የቦርድ ሃላፊዎች ያሉበት ስብሰባ ብዙ ጊዜ ይወስዳል” ማለታቸውም የሚታወስ ነው፡፡

ይህን ተከትሎም በርካታ ትችት ሲያስተናግዱ ቆይተዋል፡፡

ወቀሳውን ተከትሎም ሃላፊው በይፋ ይቅርታ ጠይቀው ነበር፡፡

በወቅቱም ዋናው ነገር ኦሊምፒኩን በጊዜው ማዘጋጀት እንጅ የእርሳቸው ጉዳይ ለውድድሩ እንቅፋት ሊሆን እንደማይገባም ገልጸዋል፡፡

ሃላፊነታቸውን ከለቀቁ በኋላም ንምግግራቸው አግባብ እንዳልነበር የተናገሩት ዮሺሮ ሞሪ ከንግግራቸው በኋላም ከቤተሰቦቻቸውም ከባድ ቁጣና ውግዘት ማስተናገዳቸውን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version