የሀገር ውስጥ ዜና

የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 ቀን ይሰጣል

By Tibebu Kebede

February 11, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 ቀን እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2013 ዓ.ም የዲጂታል መታወቂያ ይሰራጫልም ብሏል።

የፈተናው ገለጻ የካቲት 26 ቀን ተካሂዶ ፈተናው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥም ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በቀጥታ (ኦንላይን) ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥም የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ በትግራይ ክልል የሚገኙ ከ12ሺ ህ በላይ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በአካባቢው የትምህርት መሰረተ ልማቶች ሙሉ ለሙሉ በመውደማቸው ፈተናቸውን በአካባቢያቸው በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚወስዱ ገልፀዋል፡፡

በምስክር ስናፍቅ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!