ቢዝነስ

የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን ባለፉት 6 ወራት ከ17 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ

By Meseret Demissu

February 08, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣን ባለፉት 6 ወራት ከ17 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ፡፡

ባለስልጣኑ በ2013 በጀት አመት 29 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ ያለ ሲሆን በስድስት ወራት ውስጥ ከ17 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡

የክልሉ የገቢ አሰባሰብ እና የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ውይይቱም የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን፣ የዞን እና የከተማ አስተዳደር የባለስልጣን ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የኦሮሚያ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ መስከረም ደበበ መንግስት በዚህ አመት ያቀዳቸውን ስራዎች ለማሳካት ገቢ ወሳኝ ሚና እንዳለው በግምገማ መድረኩ አንስተዋል፡፡

ዘንድሮ ለማሳካት ከተያዙ ዕቅዶች መካከልም የመስኖ ልማት፣ የትምህርት ቤቶች ማስፋፊያ፣ ኮቪድን ለመከላከል እና ማህበራዊ አገልግሎትን ለማስፋት ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የገቢ አሰባሰብን ማዘመን፣ ሰራተኞችን በትጋት ማሰራት፣ በክልሉ ብዙም ሲሰራበት ያልነበረ የህንፃ ኪራይ ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ፣ ለግብር ከፋዩ ቀልጣፋ እና ምቹ አሰራርን መዘርጋት ወሳኝ የትኩረት አቅጣጫ መሆናቸውንም ነው ዋና ዳይሬክተሯ የገለጹት፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን