Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምስራቅ አፍሪካ ባንኮች መካከል የመጀመሪያውን ደረጃ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ባንኮች 1ኛ ደረጃ ደረጃ መያዙ ተነገረ፡፡

በተጠናቀቀው የአውሮፓውያን 2020 በጀት ዓመት አፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ 100 ባንኮች መካከል ደግሞ 17ኛ ደረጃ መያዙን ባንኩ አስታውቋል፡፡

ይህንን ደረጃ ያወጡት “አፍሪካ ቢዝነስ እና ዘ አፍሪካ ሪፖርት” ይፋ ባደረጉት ጥናት ነው ተብሏል፡፡

የአፍሪካ ባንኮች በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት በተከሰተው የኢኮኖሚና የንግድ መቀዛቀዝ ሳይበገሩ ከባለፉት 10 ዓመታት የተሻለ የካፒታል መጠን በማስመዝገብ ዓመቱን ማጠናቀቃቸውም ተገልጿል፡፡

ባንኮች አማራጭ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅና በዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች አማካኝነት ተደራሽነትን ለማስፋት ያደረጉት ጥረት የኮቪድ ተጽዕኖን በመቋቋም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንዳስቻላቸው የጥናት ሪፖርቶቹ አስነብበዋል፡፡

የኢትጵያ ንግድ ባንክ ከአፍሪካ ቀደምት ባንኮች አንዱ ሲሆን፣ ባለቤትነቱ የሀገር ሀብት ሆኖ በአገር ውስጥ ብቻ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በአፍሪካ ተወዳድሮ 17ኛ ከምስራቅ አፍሪካ ከ267 በላይ ባንኮች በሚገኙበት ምድብ 1ኛ መሆኑ ትልቅ ስኬት መሆኑን ባንኩ አስታውቋል፡፡

ባንኩ እየተገበረ ያለው የዲጂታላይዜሽን ስትራቴጂ የባንኩን ተደራሸነት፣ የአገልግሎ ጥራትና ቅልጥፍና በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው የሚጠበቅ ሲሆን፣ የአፍሪካ ተፎካካሪነቱን በማጠንከር አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ባንክ ለመሆን ላስቀመጠው ራዕይ ስኬትም ትልቅ ስፍራ ይኖረዋል ሲል በፌስቡክ ገጹ ገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version