የሀገር ውስጥ ዜና

34ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ተጀመረ

By Tibebu Kebede

February 06, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) 34ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀመረ።

የዘንድሮው ጉባኤ “ኪነ ጥበብ፣ ባህል እና ቅርስ የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመገንባት” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የህብረቱ መሪዎች ጉባኤ በተለያዩ አህጉራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ያደርጉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ባመጣው የማህበረ ምጣኔ ሀብት ጫናን እንዴት ማገገም እንዳለባትም ሀሳብ ቀርቦ ሊወያዩበት እንደሚችሉ እየተጠበቀ ነው።

ዘንድሮ በይፋ ወደ ተግባር የገባው አህጉራዊው ነፃ የንግድ ቀጣና ወቅታዊ አፈጻፀም ላይም ውይይት እንደሚደረግ መረጃዎች ያመላክታሉ።