በአማራ ክልል ከ40 በላይ የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት ቢኖሩም እሴት ጨምሮ ለገበያ በማቅረብ የሚገኘው ገቢ ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ከ40 በላይ የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት ቢኖሩም እሴት ጨምሮ ለገበያ በማቅረብ የሚገኘው ገቢ ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት በክልሉ በብዛት ይገኙ እንጅ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለአካባቢው ማኅበረሰብ ሆነ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡
የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አደራው ዳኛው የዓለም ባንክ ያደረገውን ጥናት ጠቅሰው እንደሚሉት በአማራ ክልል ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ከ40 በላይ የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት ይገኛሉ፡፡
ይሁን እንጅ የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናትን እሴት ጨምሮ ለገቢያ በማቅረብ የሚገኘው ገቢ ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሚዳ እምርታ ፕሮጀክት ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋም ድህነትን ለመቀነስ እየሰራ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ኢንተርፕራይዞቹ የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናትን ቆርጠው ከመሸጥ ወጥተው ጌጣጌጦችን አምርተው ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እያቀረቡ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
በማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የማዕድን ግብይት ሥራዎች ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክተር አቶ በትሩ ኀይሌ በበኩላቸው ሚዳ እምርታ ፕሮጀክት መንግሥት መሸፈን ያልቻለውን በመሸፈን ለበርካታ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች የሥራ እድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከ2010 እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ እሴት ሳይጨመርባቸው ከተላኩ የከበሩ የጌጣጌጥ ማዕድናት ሽያጭ ማግኘት ያለባትን ከ226 ሚሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማጣቷን አብመድ ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!