Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለፉት ስድስት ወራት ህግን በተላለፉ 46 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት ህግን በተላለፉ የንግድ እና የማምረቻ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባካሄደው ክትትልና ቁጥጥር ህግ ተላልፈው በተገኙ 46 ድርጅቶች ላይ ከማስጠንቀቂያ እስከ እገዳ የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን በሚኒስቴሩ የገበያና ፋብሪካ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሬ ዳይሬክተር አቶ ተከተል ጌቶ ተናግረዋል፡፡

የንግድ እና የማምረቻ ድርጅቶቹ እርምጃ የተወሰደባቸው ከተሰጣቸው የንግድ ስራ ፈቃድ ዉጪ በመነገድ፣ ባልታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ በመነገድ፣ በምርት ጥራት መጓደል እና ብሄራዊ የምልክት አጠቃቀም መመሪያን ተግባራዊ ባለማድረግ ምክንያት መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የንግድ ድርጅቶችም ሆኑ የማምረቻ ተቋማት ስራቸውን በስነ ምግባር መስራት እንዳለባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለጥራት ብሎም ለአዋጆች ተግባራዊ መሆን ልዩ ትኩረተ ሰጥቶ እንደሚሰራ የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ህግና ሥርዓትን ተላልፈው የሚሰሩ ድርጅቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version