Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከሚሳኤል ጥቃቱ በኋላ የኢራን ውድቀት  እየታየ ነው- ዶናልድ ትራምፕ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ  ኢራን በአሜሪካ የጦር መንደር ላይ ጥቃት ከፈፀመች በኋላ  ውድቀቷ እየታየ ነው ሲሉ ገለፁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ኢራን  በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር መንደር ላይ የፈፀመችውን ጥቃት በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በተፈፀመው ጥቃት  የአሜሪካም ሆነ የኢራቅ ወታደሮች ህይወት እንዳላለፈ የገለፁ ሲሆን በጦር መንደሩ ላይ በተፈፀመው ጥቃት የተወሰነ ጉዳት ብቻ መከሰቱን ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ በመግለጫቸው  አሜሪካ በኢራን ላይ በቀጥታ ተጨማሪ የፋይናስ እና የኢኮኖሚ ማዕቀብ ልትጥል እንደምትችል በመግለፅ ይህም ባህሪዋ እስካልተቀየረ ድረስ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በፊት ፕሬዚዳንቱ ኢራን የአሜሪካ የጦር መንደሮችን እና ወታደሮች ላይ ኢላማ ካደረገች ወታደራዊ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ አስጠንቅቀው የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ከዚህ አይነት አስተያየት መቆጠባቸው ተጠቁሟል፡፡

ከዚህ ባለፈ ፕሬዚዳንቱ ኢራን የኒውክሌር ጦር ባለቤት እንዳትሆን እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

Exit mobile version