የሀገር ውስጥ ዜና

በሲቲ ዞን የተገነባው የደወሌ ድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሽከርካሪ ማቆያ ተርሚናል ተመረቀ

By Meseret Awoke

January 30, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሲቲ ዞን አይሻአ ወረዳ የተገነባው የደወሌ ድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሽከርካሪ ማቆያ ተርሚናል ዛሬ ተመርቋል።

ተርሚናሉ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ፣ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ያደታ፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እንዲሁም ሌሎች የክልል እና የፌዴራል የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል፡፡

ወ/ሮ ዳግማዊት የተርሚናሉ መገንባት አሽከርካሪዎች በጂቡቲ የሚኖራቸውን ቆይታ የተሳለጠ ከማድረግ ባሻገር የሎጀስቲክ ስርዐቱ የተፋጠነና የገቢና ወጪ ንግዱ ውጤታ እንዲሆን ያደርገዋል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም 781 ኪሎ ሜትሮችን የሚሸፍነውን የትራንስፖርት ስርዓት ለመምራት እንደሚያስችል የገለፁት ወ/ሮ ዳግማዊ በመስመሩ በቀን ከ250 በላይ ተሽከርካሪዎች የሚመላለሱበት በመሆኑ በቀጣይ ተርሚናሉ መሰረተ ልማቱ በሙሉ ሲሟላለት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚሰጥ ገልፀዋለወ።

ተሾመ ሀይሉ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!