አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ፣ ላይቤሪያና ማልታ የዓለም አቀፉ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን አዲስ አባል ሃገራት በመሆን ተቀላቀሉ።
ምርጫው የአባል ሃገራቱን ቁጥር 95 እንዳደረሰውና ከአፍሪካ አስራ አራት እንዲሁም ከአውሮፓ ሰላሳ አምስት ሃገራትን አባል አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ነው ተብሏል።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኡልፍ መህረንስ ዓለም ካለችበት ፈታኝ ሁኔታ አኳያ ፌዴሬሽኑ አዳዲስ አባላትን እያካተተ በመምጣቱ ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸው ትኩረት ባደረጉበት በአፍሪካ አህጉር የበለጠ ተሳትፎ መታየቱ የሚያበረታታና በአህጉሪቱ እየተሰራ ላለው ስራም ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
“ሃገራቱን እንኳን ወደ ፌዴሬሽ መጣችሁ ማለት እፈልጋለሁ” ያሉት ፕሬዚዳንቱ በዊልቼር ቅርጫት ኳስ መስክ ሃገራቱን ከማሳተፍ ባሻገር ስኬት እንዲያመጡ በጋራ እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ከኢዜአ ዘግቧል።
የትኛውም የአፍሪካ ሃገር በዊልቼር ቅርጫት ኳስ ሜዳሊያ አግኝቶ እንደማያውቅ ያስታወሰው የኢንሳይድ ዘጌምስ ዘገባ ጃፓን ባዘጋጀችውና በኮቪድ ምክንያት አንድ ዓመት በተራዘመው የ2020 ፓራሊምፒክ ላይ የአልጄሪያ ዊልቼር ቅርጫት ብሄራዊ ቡድን በሁለቱም ጾታ እንደሚሳተፍ ይጠበቃል ብሏል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!