Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢራን በአሜሪካ የጦር መንደር ላይ ጥቃት ከፈፀመች በኋላ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀቡ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን ኢራቅ በሚገኙ ሁለት የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት መፈፀሟን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ከፍ ማለቱ ተሰምቷል፡፡

በዚህም ያልተጣራ አንድ በርሚል የነዳጅ ዘይት በ1 ነጥብ 4 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በመካከለኛው እስያ በ69 ነጥብ 21 ዶላር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

ወርቅ እና የጃፓን የን የመሳሰሉ የመገበያያ ገንዘቦች ላይም ጭማሪ መታየቱ ነው የተነገረው፡፡

በተመሳሳይ በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት እየነገሰ መምጣቱን ተከትሎ የዓለም አቀፉ አክሲዮን ገበያ ዝቅ ማለቱ ተመላክቷል፡፡

የጃፓኑ የኒኬል 225 ግብይት በ1 ነጥብ 3 በመቶ እና የሆንግ ኮንጉ ሃንግ ሴንግ ደግሞ በ0 ነጥብ 8 በመቶ ቀንሷል፡፡

ኢራን የፈፀምኩት የባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃት በአሜሪካ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ለተገደሉት ጄኔራል ቃሲም ሱለይማኒ የብቀላ እርምጃ ነው ብላለች፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Exit mobile version