አዲስ አበባ ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአትሌቲክስ ዳኛና አሰልጣኝ አቶ እሸቱ በዩ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
አቶ እሸቱ በዩ ባደረባቸው ህመም ምክንያትበየካቲት 12 ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትላንት ጥር 20 ቀብ 2013 ዓ.ም. ሌሊት ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።
በኢትዮጵያ አትሌቲክስ እድገትና ውጤታማነት ላይ ከፍ ያለ ሚና እንደነበራቸው ነው ፌዴሬሽኑ ያስታወቀው።
አቶ እሸቱ በዩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዳኞች ማህበር ፀሐፊ በመሆን፣ በተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይም ለረዢም አመታት በዳኝነት ሥራ ተሰማርተው የኢትዮጵያን አትሌቲክስ በማሳደግ ረገድ ከፍ ያለ ድርሻ እንደነበራቸው ተጠቁሟል።
በአትሌቲክስ ዳኝነት ስልጠና ሥራም በርካታ ወጣት ዳኞችን በማፍራት ጉልህ ሚና ያበረከቱና በኦሮሚያ ክልል የአትሌቲክስ ዳኞች ማህበር እንዲመሰረት ከማድረግ ጀምሮ በአመራርነት ያገለገሉ ነበሩ ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ዳኛ አቶ እሸቱ በዩ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!