የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ ሰብአዊ መብት ረዳት ዋና ጸሀፊ ኢልዜ ብራንድስ ኬህሪስ ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

January 29, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ ሰብአዊ መብት ረዳት ዋና ጸሀፊ ኢልዜ ብራንድስ ኬህሪስ ጋር ተወያዩ።

አምባሳደሩ በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት እና መሰረተ ልማቶችን መልሶ መጠገን ላይ እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ የተፈጸመ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ካለ ለመመርመር ቁርጠኛ መሆኗን አስረድተዋል።

የተመድ ኤጀንሲዎች በማማከር ስራ ላይ ቀና ትብብር እና ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!